مريم ابنت عمران عليها السلام موسوعة القرآن الكريم
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesAlms Giving [Al-Maun] - Amharic translation - Africa Academy
Surah Alms Giving [Al-Maun] Ayah 7 Location Maccah Number 107
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በምርመራው ቀን የሚያስተባብለውን ሰው አየህን? (አወከውን?)
2. ይሀውም ያ የቲምን በኃይል የሚገፈትረው፤
3. ድሃን በማብላት ላይም የማያነሳሳው ነው።
4. ወዮላቸው ለሰጋጆች፤
5. ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለሆኑት (ሰጋጆች)፤
6. ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለሆኑት፤
7. የዕቃ ትውስትንም ሰዎችን የሚከለክሉ ለሆኑት ሁሉ ወዮላቸው::

