لَّقَدۡ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓاْ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡمَسِيحُ ٱبۡنُ مَرۡيَمَۚ قُلۡ فَمَن يَمۡلِكُ مِنَ ٱللَّهِ شَيۡـًٔا إِنۡ أَرَادَ أَن يُهۡلِكَٱلۡمَسِيحَ ٱبۡنَ مَرۡيَمَ وَأُمَّهُۥ وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗاۗ وَلِلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَاۚ يَخۡلُقُ مَايَشَآءُۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
الأمهرية | አማርኛ
ከክርስቲያኖች መካከል እነኛ አላህ ማለት እራሱ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ ነው ያሉትበርግጥ ክደዋል። አንተ መልእክተኛ ሆይ! አላህ የመርየም ልጅ መሲሕን፣ እናቱን መርየምንእና በምድር ላይ ያሉትን ፍጡራን በሙሉ ሊያጠፋቸው ቢፈልግ ሊያድናቸው የሚችለውማነው? በላቸው። እናም አላህ ይህንን ከማድረግ የሚከለክለው አንዳችም አካል አለመኖሩከርሱ በቀር በእውነት ሊመለክ የሚገባ ሌላ አምላክ እንደሌለ ያስረዳል። እንዲሁምሁላቸውም፣ ዒሳ (ዐለይሂ አሰላም) እናቱም መርየም እና በምድር ላይ ያሉ ፍጡራን በሙሉየአላህ ባሮች መሆናቸውን ይጠቁማል። የሰማያቱ፣ የምድሩ እና በመሀከላቸው ያሉ ነገሮችንግሥና ሁሉ የአላህ ነው። የፈለገውን ይፈጥራል። ሊፈጥራቸው ከፈለጋቸው እናከፈጠራቸው አካላት መካከል ደግሞ የአላህ ባሪያ እና መልእክተኛው የሆነው ዒሳ (ዐለይሂአሰላም) ይገኝበታል። አላህም ሁሉን ነገር ቻይ ነው።
مَّا ٱلۡمَسِيحُ ٱبۡنُ مَرۡيَمَ إِلَّا رَسُولٞ قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِهِ ٱلرُّسُلُ وَأُمُّهُۥ صِدِّيقَةٞۖ كَانَا يَأۡكُلَانِ ٱلطَّعَامَۗ ٱنظُرۡكَيۡفَ نُبَيِّنُ لَهُمُ ٱلۡأٓيَٰتِ ثُمَّ ٱنظُرۡ أَنَّىٰ يُؤۡفَكُونَ
الأمهرية | አማርኛ
የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ ከርሱ በፊት እንዳለፉት መልእክተኞች አንድ መልዕክተኛእንጂ ሌላ አይደለም። በነርሱ ላይ የደረሰው ሞትም እርሱን በጊዜው ያገኘዋል። እናቱምመርየም የአላህን አምላክነት ያረጋገጠች እውነተኛ የአላህ ባሪያ ነች። ምግብየሚያስፈልጋቸውም ሰብዓዊ ፍጡራን በመሆናቸውም ምግብ ይበሉ ነበር። እናም ምግብየሚበላ አካል እንዴት ሊመለክ ይገባል? አንተ መልእክተኛ ሆይ! የአላህን አንድነት የሚያሳዩ፣እንዲሁም የሌሎች አምላክነትን ውድቅ የሚያደርጉ አንቀፆችን እንዴት እንደምናብራራተመልከት። እንዲህ ከመሆኑ ጋር እነኚህን አንቀፆች ይቃወማሉ ከዚያም ከእነኚህ ግልፅአንቀፆች ጋር እንዴት ከእውነት እንደሚዘነበሉ ተመልከት።
إِذۡ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَى ٱبۡنَ مَرۡيَمَ ٱذۡكُرۡ نِعۡمَتِي عَلَيۡكَ وَعَلَىٰ وَٰلِدَتِكَ إِذۡ أَيَّدتُّكَ بِرُوحِ ٱلۡقُدُسِ تُكَلِّمُ ٱلنَّاسَفِي ٱلۡمَهۡدِ وَكَهۡلٗاۖ وَإِذۡ عَلَّمۡتُكَ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَٱلتَّوۡرَىٰةَ وَٱلۡإِنجِيلَۖ وَإِذۡ تَخۡلُقُ مِنَ ٱلطِّينِ كَهَيۡـَٔةِ ٱلطَّيۡرِبِإِذۡنِي فَتَنفُخُ فِيهَا فَتَكُونُ طَيۡرَۢا بِإِذۡنِيۖ وَتُبۡرِئُ ٱلۡأَكۡمَهَ وَٱلۡأَبۡرَصَ بِإِذۡنِيۖ وَإِذۡ تُخۡرِجُ ٱلۡمَوۡتَىٰ بِإِذۡنِيۖ وَإِذۡكَفَفۡتُ بَنِيٓ إِسۡرَـٰٓءِيلَ عَنكَ إِذۡ جِئۡتَهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡهُمۡ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٞ
الأمهرية | አማርኛ
አንተ መልእክተኛ ሆይ! አላህ የመርየምን ልጅ ዒሳን (ዐለይሂ አሰላም)፡– <<አንተ የመርየምልጅ ዒሳ ሆይ! አንተን ያለ አባት በፈጠርኩህ፣ እናትህንም መርየምን በርሷ ዘመን ከነበሩሴቶች ሁሉ በመረጥኳት፣ በቅዱሱ መንፈስም በጂብሪል ባበረታሁህ፣ ሰዎችንም ወደ አላህመንገድ የምትጠራቸው ስትሆን በልጅነትህ በምታናግራቸው፣ በጎልማሳነትህም ወቅትአላህ ወደነርሱ በላከህ ነገር የምትናግራቸው ስትሆን ፅሑፍን ባስተማርኩህ፣ በሙሳም ላይያወረድኩትን ተውራትን ባስተማርኩህ፤ ባንተም ላይ የተወረደውን ኢንጂልን ባስተማርኩህእና የሸሪዓውን ሚስጥር፣ ህግጋት እና ጥበቦቹንም ባስተማርኩህ፣ ከጭቃም አድቦልቡለህእስትንፋስን ስትነፋበት በፍቃዴ በራሪ ወፍ በሚሆንበትም፣ ዓይነ ስውርንሁኖየተፈጠረውን ሰዉ ም በፍቃዴ በምታሽርበት፣ ለምፃንም በመዳበስ ከለምፁ ድኖ ባለመልካም ቆዳ በሚሆን ጊዜ አሏህን በመማጸን ሙታንንም በምትቀሰቅስ ጊዜ ይሄ ሁሉ በኔፈቃድ ሲሆን የዋልኩልህን መልካም ፀጋዬን አውሳ። የኢስራኤል ልጆችንም ግልፅ በሆኑተዓምራትን ይዘህ በመጣህላቸው ጊዜ በተዓምራቱ ክደው ሊገድሉህ ሲፈልጉእንዳይደርሱብህ ካንተ ከለከልኳቸው። ተዓምራቱንም ባዩ ጊዜ እነኛ ከሀዲያን ይህ ግልፅየሆነ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም አሉ።
وَإِذۡ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَى ٱبۡنَ مَرۡيَمَ ءَأَنتَ قُلۡتَ لِلنَّاسِ ٱتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَٰهَيۡنِ مِن دُونِ ٱللَّهِۖ قَالَ سُبۡحَٰنَكَمَا يَكُونُ لِيٓ أَنۡ أَقُولَ مَا لَيۡسَ لِي بِحَقٍّۚ إِن كُنتُ قُلۡتُهُۥ فَقَدۡ عَلِمۡتَهُۥۚ تَعۡلَمُ مَا فِي نَفۡسِي وَلَآ أَعۡلَمُ مَا فِينَفۡسِكَۚ إِنَّكَ أَنتَ عَلَّـٰمُ ٱلۡغُيُوبِ
الأمهرية | አማርኛ
አላህም በፍርዱ ዕለት ዒሳን (ዐለይሂ አሰላም) ሲያናግረው አውሳ። > ይለዋል። ዒሳም(ዐለይሂ አሰላም) ጌታውን ሲያጠራ፡– > ይላል።
